Fana: At a Speed of Life!

አሁን ገንዘብ ሳይሆን ሀገር እና ህዝብ የምናተርፍበት ጊዜ ነው- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚስተዋለውን የኢኮኖሚ አሻጥርና ህገወጥ ተግባራት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በስራ ላይ ያለው የቁጥጥር ግብረሃይል የስራ አፈጻጸም ተገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የቁጥጥር ግብረሃይሉ ሰብሳቢ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ግብረሃይሉ ባለፉት ቀናት ባካሄደው የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች በአጠቃላይ የግብይት ስርዓቱን ማረጋጋት ተችሏል ብለዋል፡፡

በተለይ መሰረታዊ የምግብ እና የፍጆታ እቃዎች አቅርቦትን በማሻሻል የገበያ ዋጋ እንዲረጋጋ አበረታች እና ተስፋ ሰጪ ውጤት ተገኝቷል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እነዚህ ውጤቶች ቢገኙም አሁንም ህገወጥነትን በመቆጣጠር ፣የኢኮኖሚ አሻጥሩን በዘላቂነት መግታት ፣ሌብነት፣ መልካም አስተዳደር ፣የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ የሚያውኩ እና ጫና የሚፈጥሩ ተግባራትን ከመፍታት እንጻር አሁንም በርካታ ስራዎች እንደሚቀሩ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አመልክተዋል ።

ማህበረሰቡ በከተማዋ የሚታየውን ማንኛውንም ህገወጥ ተግባር ለመከላከል በ9977 ነጻ የስልክ መስመር እና በከንቲባ ጽሕፈት ቤት አራተኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ጥቆማ መስጠት የሚችል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.