Fana: At a Speed of Life!

በዳባት ቆርጦ የገባው የህወሓት ታጣቂ ተመቶ እየተመለሰ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዳባት ወረዳ ቆርጦ የገባው አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ቡድን ተመቶ እየተመለሰ መሆኑን የዳባት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም ገለጹ።

አራተኛ ቀኑን በያዘው ውጊያ አሻባሪው የህወሓት ቡድን እየተደመሰሰ መሆኑን አስተዳዳሪው አመላክተዋል።

በወረዳው አጅሬ ጃኖራ ቆርጦ የገባው ሃይል በመከላከያ፣ በልዩ ሃይል፣ በፋኖና በማህበረሰቡ መመታቱን አስረድተዋል።

አያይዘውም ቡድኑ በውቅን በኩል ቆርጦ ለመውጣት ሲሞክር እየተመታ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ተስፋ የቆረጠው ሃይል ነዋሪውን ለመረበሽ እየተኮሰ ነው ያሉት አስተዳዳሪው ህብረተሰቡ ተረጋግቶ መደበኛ ስራውን እንዲሰራና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅም ጥሪ አቅርበዋል።

የአሸባሪው ቡድን አሁን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑንም አስተዳዳሪው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ገልጸዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በስልክ ባደረሱን መረጃ ማህበረሰቡ ተረጋግቶ አካባቢውን እየጠበቀና ከጸጥታ ሃይሉ ጎን መቆሙን አረጋግጠዋል።

በሰላም አስመላሽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.