Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው 78 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ከአሸባሪው የህውሓት ቡድን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው 78 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷የጁንታው ተላላኪዎች ወደ ከተማዋ ሰርገው በመግባት የሽብር ጥቃት እንዳይፈጽሙ ጠንካራ
የኬላ ፍተሻና የጸጥታ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡

በጎንደር ከተማ 78 ዋና የጁንታው አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ያለት ሃላፊው ÷ ሌሎች 58 ተጠርጣሪ የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች መያዛቸውንም አንስተዋል።

የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎችን ከመከላከል ባለፈ ለጁንታው መረጃ በመስጠት እና በፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ መረጃ የተገኝባቸው የውስጥ ባንዳዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት ፡፡

ወደ ከተማዋ ሰርጎ በመግባት ጥፋት ለመፈጸም ጥረት የሚያደርጉ የጁንታው ተላላኪዎችን በማጋለጥ ረገድ የከተማው ህዝብ እያደረገ ያለው ተሳትፎ ፍሬያማ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለስራው ውጤታማነትም ወጣቶች በአደረጃጀታቸው የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ በሮች ተመሳስለው የሚገቡ የጥፋት ሃይሎች ስለሚኖሩ የከተማው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.