Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ሴቶችና ህጻናት ሰለባ ናቸው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ሴቶችና ህጻናት ሰለባ በመሆናቸው መላው ኢትዮጵያውያን በጋራ ልንመክተው ይገባል ሲሉ የቤንች ሸኮ ዞን ሴቶች ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና የህወሓት አሸባሪ ቡድንን የሚያወግዝ ሠልፍ በቤንች ሸኮ ዞን እየተካሄደ ነዉ፡፡

በሠልፉ ከቤንች ሸኮ ዞን ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ሴቶች ተሣታፊ ሆነዋል፡፡

በሚዛን አማን ከተማ በተደረገው ሠልፍ ”ሴቶች የሠላም ተምሣሌት እና የጥንካሬ መገለጫ ናቸዉ፤ አሁን ላይ እንደ ሀገር ያጋጠመንን የዉስጥ እና የዉጭ ጫና ለመታገል እና አብሮነትን ለማሥቀጠል ቁርጠኞችም ነን” ብለዋል፡፡

አሸባሪዉ ህዉሓት እስከ መጨረሻው ከኢትዮጵያ እስኪጠፋ በግንባር በመሠለፍም ሆነ ሥንቅ በማዘጋጀት አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሪት ወርቅነሽ ባድንሥ ÷ እኩል ተጠቃሚነትን እንደ ሽንፈት የቆጠረዉና በስልጣን ጥም የናወዘዉ ህዉሓት የሀገር መከላከያን በመዉጋት በአማራ እና አፋር ክልሎች ጦርነትን በማስፋት ለሰብዓዊነት ግድ እንደሌለዉ አሳይቷል ብለዋል፡፡

ለጥቃት እና ጦርነት ሠለባ የሆኑት ሴቶች እና ህፃናት በመሆናቸው ኢትዮጵያዊያን በዚህ ወቅት ልንተባበር ይገባናልም ነው ያሉት፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ህዝብ ሃገርን ለመታደግ ግንባር በመዝመት፣ ደም በመለገስ፣ ስንቅ በማዘጋጀትና በሌሎችም ድጋፎች ከሰራዊቱ ጎን መሆኑን እየገለፀ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

በተመስገን ይመር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.