Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ የጫት መቃሚያ እና የሽሻ ማስጨሻ ቤቶች ተዘግተው ወጣቶች አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ተጠየቀ።

ከተማ አስተዳደሩ ከንግዱ ማሕበረ-ሰብ ጋር ባደረገው ውይይት ወጣቱ ከጫት ሱስ ወጥቶ የህልውና ዘመቻውን እንዲቀላቀል የጫት መቃሚያ እና የሽሻ ማስጨሻ ቤቶች እንዲዘጉ በተጠየቀው መሰረት ከዛሬ ጀምሮ እርምጃው ይወሰዳል ተብሏል።

ከንቲባው አቶ አበበ ገ/መስቀል በህብረተሰብ ትብብር እነዚህን ንግድ ቤቶች እንዘጋለን ብለዋል።

በከተማዋ ትናንት ብቻ 8 ጸጉረ ልውጦች መያዛቸውን የገለጹት ከንቲባው ወጣቱ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ለመከላከያ ለልዩ ሀይል እና ሚሊሻ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ከመጪው ሐሙስ ጀምሮ ነጋዴው ማህበረሰብ ግንባር ድረስ በመገኘት እገዛ ማድረግ እንደሚጀምርም ከንቲባው ገልፀዋል፡፡

በሰብለ ሲሳይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.