Fana: At a Speed of Life!

የሕይወት መስዋእትነት ለከፈሉ የጀግኖች የቤተሰብ አባላት የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ ባለሃብት አቶ አሕመድ ኑሩ ለሕዝብ ሲሉ መስዋእትነት ለከፈሉ ጀግኖች ክብር ይገባቸዋል፤ ታሪክም ሲዘክራቸው ይኖራል ብለዋል።

የጀግኖችን ቤተሰብ ማገዝ ከሁሉም የአማራ ሕዝብ የሚጠበቅ ተግባር ነው ያሉት ባለሃብቱ አቶ አሕመድ፥ በጎንደር ከተማ ለሚኖሩ የሕይወት መስዋእትነት ለከፈሉ የጀግኖች ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው የ140 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

አስተያየታቸውን  የሰጡ የጀግኖች ቤተሰብ አባላት አርበኛ ገበየሁ እንየው  “ወንድሜ ለሕዝብ ክብር ሲል ቢሰዋም ለቤተሰቡ እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ ነው” ብሏል።

ሌላኛዋ ድጋፍ የተደረገላቸው  ወይዘሮ ሰርካለም ቦጋለ “ባለቤቴ ሕዝብን በማስቀደም ቢሰዋም እንደ አቶ አሕመድ ኑሩ አይነት ግለሰቦች አይዟችሁ እያሉን ነው፤ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” ብለዋል።

ጀግኖቹ የተሰውለት የሕዝብ ክብር እንዲጠበቅ ሁሉም ኀላፊነቱን በመወጣት የሕልውና ዘመቻውን መቀላቀል አለበት  ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.