Fana: At a Speed of Life!

እውነታውን ለአለምና ለአፍሪካውያን ለማድረስ የትዊተር ዘመቻውን መቀላቀል ይገባል -አምባሳደር አለምጸሀይ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኡጋንዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

ከምናደርገው የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪም እውነታውን ለአለም ህብረተሰብና ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ለማድረስ የትዊተር ዘመቻውን በትኩረት መቀላቀል ይገባናል ሲሉ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት ተናግረዋል።

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ2ኛ ዙር ሁለንተናዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የመክፈቻ መርሃግብር ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ትዕቢት የተከፈተብንን ወረራ ለመመከት በግንባር እየተዋደቀ ካለው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ጎን እንቆማለን ሲሉ ገልጸዋል።

በወቅቱም በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት ባደረጉት ንግግር፥ የህወሃት አሸባሪ ቡድን በጥቅምት ወር በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን አሳፋሪ ጥቃት አስታውሰዋል።

አሁንም መንግስት የወሰደውን የተናጥል የተኩስ አቁም ርምጃ በመናቅ ህፃናት ወደ ጦርነት እየማገደ የአማራና የአፋር ክልሎች የሚገኙ ንፁሃን ዜጎችን በግፍ ማጥቃቱን፣ የግል ንብረት ሳይቀር የአለምአቀፍ ህጎች በመጣስ የህክምና መስጫን ጨምሮ መሰረተ ልማቶችን ማውደሙን ገልፀዋል።

ይህን እኩይ ተግባር ሁሉም ሊያውግዘው የሚገባ ሲሆን÷ አሸባሪ ቡድኑን ለመመከት በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቀው በጋራ ቆመዋል ብለዋል።

በተጨማሪም እያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በያለበት የሰራዊቱ ደጀን በመሆን ሀገርን መጠበቅ ግዴታው እንደሆነም አምባሳደሯ ገልፀዋል።

በዕለቱ የተገኙ ተሳታፊዎች የህወሓት ከፋፋይ ስርዓት ማክተሙን ተከትሎ፥ ቡድኑ በእኩይ ተግባር ሀገርን እና ህዝብን ወደ ጦርነት መክተቱትን በማውገዝ በዚህ ወሳኝ ወቅት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በውጭ የምንገኝ ወደ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ስንልክ በባንክ በኩል በመላክ አሸባሪ ቡድኑ የሚያደርገውን የኢኮኖሚ አሻጥር መከላካል ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም አምባሳደሯ በኡጋንዳ የሚገኙ የኮሚኒቲው አባላት ከወራት በፊት በመጀመሪያ ዙር ለመከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን፣ የኮቪድ -19 በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያደረሰው ከባድ ጫና በመቋቋም ላደረጉት የ24 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ለ2ኛ ጊዜ ድጋፍ የማሰባሰቢያ ስራ መቀጠሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.