Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የሚካሄደው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል የሚካሄደው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ የሚገኙ የመንግስትና የፀጥታ አካላት አመራሮች በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ናስር ዩያ እንደገለጹት÷ ምርጫው ሰላማዊ ፍትሀዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በተለይም ወረዳዎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር በትኩረት መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ ማንሳታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘከሪያ ÷በክልሉ በአሁኑ ወቅት እየታየ የሚገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጠናር የክልሉ ፖሊስ በትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ያሉ ሲሆን በተለይም በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ና በሀላፊነት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.