Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ የሜካናይዝዱና የእግረኛ ተዋጊዎች ጥምረት ጉልህ ነው- ብርጋዴር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)”አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ የሜካናይዝዱና የእግረኛ ተዋጊዎች ጥምረት ጉልህ ነው ሲሉ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ገለጹ።
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ በሚል ቅዠት ከተደበቀበት ዋሻ በመውጣት በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም በንፁሃን ዜጎችና በንብረት ላይ ውድመት እየፈፀመ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫፍ ጫፍ በመነሳት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን የህወሓት የሽብር ቡድን እስከ መጨረሻው ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በጋራ ተነስተዋል።
ብርጋዴር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ይህ ወራሪ ኀይል ሰርጎ በገባባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ሽንፈትና ኪሳራ ደርሶበታል ብለዋል።
ለዚህ ድል መገኘት ደግሞ የሜካናይዝዱና የእግረኛ ተዋጊዎች ጥምረት ጉልህ ነው ብለዋል።
ኮሎኔል ዘለቀ አለባቸው የጨጨሆ ግንባር የሜካናይዝድ ክፍሎች አስተባባሪ እንዲሁም የአየር ኀይል እና የምድር ኀይል አስተባባሪ እንደገለፁት፥ የእግረኛ ተዋጊዎች እና የሜካናይዝድ ክፍሉ በከፍተኛ የውጊያ ጥበብ በመመራቱ ወራሪው ኀይል ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት የዘረፈውን ንብረት ጥሎ እየፈረጠጠ ነው እኛም እየተከተልን እየደመሰስነው እንገኛለን።
ህዝብም በየአካባቢው እየሸሸ የሚመጣውን ጠላት በመፋለም ታሪክ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ኮሎኔል ወርቁ አሸናፊ የ5ኛ ሜካናይዝድ ኦፕሬሽናል ምክትል አዛዥ በበኩላቸው፥ ይህን የሽብር ቡድን የምንዋጋው ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ለመጠበቅ ነው።
እኩይ አላማን ተሸክሞ የሚንቀሳቀሰውን ጠላት በአጭር ጊዜ ለመቅበር ደግሞ በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የእያንዳንዱ ድል ባለቤት የሆነው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን ሆኖ እያደረገ ላለው ድጋፍ እናመሰግናለን።
ይሄን አውዳሚ ቡድን በአጭር ጊዜ በማጥፋት ለህዝባችን የድል ዜና እናበስራለን ማለታቸውን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.