Fana: At a Speed of Life!

የሰፈራ ጣቢያዎችን የመሰረተ ልማት ፍላጎቶች ለማሟላት ባለድርሻ አካላት ሊደግፉ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በየአካባቢው የሚገኙ የሰፈራ ጣቢያዎችን የመሰረተ ልማት ፍላጎቶች ለማሟላት በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት ሊደግፉ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የካፋ ዞን ሺሾእንዴ ወረዳ አስተዳደር በባለድርሻ አካላት በወረዳው አዲስ የተቋቋሙትን ሕሪዮና ሸመሮ የሰፈራ ጣቢያዎችን አስጎብኝቷል፡፡

ሁለቱም ሰፈራ ጣቢያዎች በቀበሌነት እንዲደራጁም ተወስኗል፡፡

የወረዳው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሰረስ አሰፋው በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት÷ የወረዳው ህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋጥ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሕሪዮና ሽመሮ የሰፈራ ጣቢያም ከ700 በላይ ስራ አጥ ወጣቶችን በማስፈር የተረጋጋ ኑሮ እንዲመሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሰፈራ ጣቢያዎች አካባቢ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ክፍተቶችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት አቶ አስረስ÷ በጉብኝቱ የተሳተፉ የዞን ባለድርሻ አካላት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰፈራ ጣቢያውን የጉበኝት የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳደር አቶ በላይ ተሰማና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በበኩላቸው፥ወጣቶች ያሉባቸውን የመሰረተ ልማት ችግሮች ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓትንና ሸኔን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ከልማቱ ጎን ለጎን ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውንም ወጣቶች ተናግረዋል፡፡

ጤፍ፣ ማሸላ፣ በቆሎ፣ ገብሰ፣ ለውዝ እና ሌሎች ሰብሎችን በቀበሌዎች በሰፋት እንደሚደርስ መግለጸቸውን ከደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.