Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍ ይቅር ሊባል አይችልም- አቶ ታዬ ደንደኣ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍ በየትኛውም መመዘኛ ይቅር ሊባል የማይችል መሆኑን በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል ካሉት 21 ዞኖችና 28 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት በወቅታዊ ሁኔታዎችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ዛሬ በአዳማ መክረዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ በወቅቱ እንዳሉት÷ የኦሮሞ ህዝብ ወያኔ ለ27 ዓመት ካደረሰበት ግፍና መከራ አልዳነም፤ አሁንም እያንዳንዱ የኦሮሞ ህዝብ ቁስል አለበት።

“ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍ በየትኛውም መመዘኛ ይቅር ሊባል የማይችል ነው” ያሉት አቶ ታዬ÷ በተለይም በኦነግ ስም የተገደለ፣ የተኮላሸና የተፈናቀለ ኦሮሞ ግድ ሳይሰጠው ቡድኑ አሁንም ለአሸባሪው ህወሃት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ መቀጠሉ ጠላትነቱን ያስመሰከረ ነው ብለዋል።

ሸኔ”ወያኔ የኔ ስትራቴጂክ አጋር ነው”ብሎ ጥምረት መፍጠሩ የኦሮሞን ወጣቶች ይበልጥ ለትግል የሚያነሳሳ ተግባር ነው’’ ሲሉ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“ሸኔ የለበሰው ካባ ኦሮሞነት ቢሆንም አሁን በራሱ ጊዜ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ወያኔ መሆኑን በራሱ ላይ በግልፅ ያወጀ ነው” ያሉ ሲሆን÷ ሸኔ ማለት ህወሓት መሆኑን የኦሮሞ ህዝብ በግልፅ የተገነዘበበት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል።

የመድረኩ ዓላማ የክልሉ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ግልፅ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና እየተጫወቱ ያሉትን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ያለመ መሆኑን አቶ ታዬ አመልክተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.