Fana: At a Speed of Life!

ሾላ ገበያ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ህንጻ ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሾላ ገበያ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ህንጻ ግንባታ እየተከናወነ ነው።

ህንጻው ከመሬት ስር የሚገነቡ ሁለት ወለሎች እና ከመሬት በላይ አምስት ወለሎች ሲኖሩት፥ በአሁኑ ወቅት ከመሬት በታች ያለው የአንዱ  ወለል ንጣፍ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

እያንዳንዱ ወለል በአማካኝ 142 የተለያየ መጠን ያላቸውን ተሽከርካሪዎች የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን፥ በአጠቃላይ 1 ሺህ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የማስተናግድ አቅም ይኖረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ በአካባበቢው ላይ የሚስተዋሉትን የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግሮች በመቅረፍ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል፡፡

መሰረተ ልማቱ ዘመናዊ የደህንነት መቆጣጠሪያ እና የተሽከርካሪ አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎች ተግባራዊ የሚደረጉበት ይሆናል፡፡

ፕሮጀክቱ በሚጠቀመው ቴክኖሎጂ፣ በመሬት አጠቃቀም ዘዴ እና ከሚያስተናግደው የተሽከርካሪ መጠን አንጻር ለከተማችን ሞዴል ፕሮጀክት ያደርገዋል ተብሏል፡፡

አካባቢው የከተማዋ ሁለተኛው ትልቅ የገበያ ማእከል እንደመሆኑ መጠን፣ ፕሮጀክቱ በዙሪያው ያሉትን የመንገድ ዳር ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎቶችን በማስወገድ መንገዶች ባላቸው ሙሉ ስፋት ልክ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያስተናግዱበትን አቅም ይፈጥራል፡፡

በፕሮጀክቱ ግንባታ ወቅት ከ120 ላላነሱ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፥ ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ደግሞ ከ80 ላላነሱ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ 530 ሚሊየን ብር ወጪ በከተማ አስተዳደሩ የተሸፈነ  መሆኑን ከትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.