Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኖች የሚያሰራጩትን አሉባልታ በጋራ መመከት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር አደኤላ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን መካከል የሚታዩ ግጭቶችን በዘላቂነት መፍታት በሚቻልበት ዙሪያ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች የተሳትፉበት ውይይት በሸዋ ሮቢት ከተማ ተካሂዷል።

በአዋሳኝ ቦታዎች በግለሰቦች መካከል የሚነሱ ግጭቶችን በማሳደግ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ የሚሰራጩ አሉባልታዎችን በጋራ መመከት እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።

በመከላከያ እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል ልዩነት እንዲፈጠር ለማድረግ በግልጽ የሚታይ የአሸባሪዎች እንቅስቀሴ እንዳለም የአካባቢው አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ጠቁመዋል።

የአካባቢው ኮማንድ ፖስት ተወካይ አሰተባባሪ ኮለኔል ተከተል ልኬ ፥ መከላከያ የሁለቱን ህዝቦች ሰላም ለማስጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት በጁንታውና በተላላኪዎቹ የሚነዙ የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎችን ህዝቡና አመራሩ መመከት ይኖርበታል ብለዋል።

የሚደረገው እርቀ ሰላም መሬት ወርዶ ተግባራዊ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ አካባቢው የሽብርተኛ ባንዳዎች ትርፍ እናገኝበታለን ብለው የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ በትብብር መስራትና ብቁ አመራር መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታትም የአካባቢው አመራሮች የጀመሩት መተማመንን መሰረት ያደረገ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውንም የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.