Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ በአሸባሪው ወረራ ለተፈናቀሉ አንድ ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ-መስቀል ማህበር አሸባሪው ህወሀት በፈፀመው ወረራ ተፈናቅለው በደባርቅ ጊዚያዊ መጠለያ ለሚገኙ አንድ ሺህ አባወራዎች አልሚ ምግብና የቤት መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
በማህበሩ የጎንደር ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አታለል ታረቀኝ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ማህበሩ በወረራው ከቤትና ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ የተደረገላቸው ከአዲ አርቃይ፣ ማይጸምሪና ዛሪማ አካባቢዎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያው ለሚገኙ አባወራዎችና ቤተሰቦቻቸው ነው።
ከተደረገው ድጋፍ መካከል ለእናቶችና ህጻናት 338 ካርቶን ሃይል ሰጪ ብስኩት ይገኝበታል፡፡
እንዲሁም ለቤት መገልገያ የሚያውሉት አንድ ሺህ የውሃ መቅጃ ጀሪካኖች፣ 2ሺህ ባልዲዎችና የልብስ ማጠቢያዎችና ከአንድ ሺህ በላይ የ ሳሙናዎች ማከፋፋላቸውንም አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.