Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ጎጃም ዞን ለሰራዊት አባላት እና ለላይ ጋይንት ማህበረሰብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን በግንባር ለሚገኙ የሰራዊት አባላት እና ወድመት ለደረሰበት ለላይ ጋይንት ማህበረሰብ ድጋፍ አድርጓል።

በዞኑ የሚገኙ 21 ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ ድጋፍ የተገኘ ሲሆን፥ 182 ሰንጋ በሬዎችን በጋይንት ግንባር እና በዋግ ግንባር ለሚገኙ ለመከላከያ ሰራዊቱ፣ ለልዩ ሐይል፣ ለፍኖ እና ለሚሊሻ አባላት ድጋፍ ተደርጓል።

በነፍስ መውጫ ከተማ ርክክብ የተደረገ ሲሆን፥ በላይ ጋይንት ወረዳ ውድመት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ አባላት 700 ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ ተደርጓል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስሜነህ አያሌው፥  ሽብርተኛው ትህነግ ሀገር ለማፍረስ ቆርጦ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ጥፋቶችን አድርሷል ብለዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የጋይንት ግንባር አስተባባሪ ብርጋዴል ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ፥ ህዝቡ የማይነጥፍ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ለሰራዊቱ ትልቅ ብርታት ሆኖታል ነው ያሉት።

በህዝቡ ደጀንነት አሸባሪው ትህነግ በዚህ ግምባር አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን አንስተዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ፥  በህወሓት ሴራ አንድነቱን ለመበተን የተሰራው  ስራ መክሸፉን እና አንድ ስንሆን ድል ከኛ ጋር ናት ብለዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ጨምሮ ሌሎች ዞኖች አያደረጉት ላለው ድጋፍም  አመስግነዋል።

በዙፍን ካሳሁን እና ምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.