Fana: At a Speed of Life!

ለዘማች ልጆች ልዩ ድጋፍ ይደረጋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት የሚዋደቁ ዘማች ልጆች በአዲሱ አዲስ ትምህርታቸው እንዲከታተሉ ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ።

ዋና አስተዳዳሪ ው ይህን ያስታወቁት  በዞኑ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የሚኖረውን የመማር ማስተማር ሂደት በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት  ጋር  በደብረ ብርሃን ከተማ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ  እንደተናገሩት፥  ሀገርን ለማዳን አሸባሪውን ቡድን የሚፋለሙ ዘማቾች ልጆች   በቀጣዩ የትምህርት ዘመን በተሟላ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ድጋፍ  ለማመቻቸት ጥረት እየተደረገ ነው።

ጥረቱን ተግባራዊ ለማድረግ ባለሀብቶችን በማነጋገር ድጋፍ ለማድረግ ከመግባባትላይ ተደርሷል ብለዋል።

ሕዝቡም የዘማች ልጆች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የዘማች ቤተሰቦችን በመንከባከብ፣  በእርሻ፣ በአረም፣ በቤት ጥገናና በገንዘብ እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.