Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ያሉ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ህወሓት በከፈተው ጥቃት ለተፈናቀሉ 530 ሺህ ብር ግምት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ አደረጉ።

የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ ወይዘሮ ዘሃራ ኡመድ ማህበረሰቡ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ አለማድረጋቸውን ተናግረው÷ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የሰብዓዊ ድጋፉ ሩዝ፣ ፓስታ፣ ዘይት እንዲሁም አልባሳትና ቁሳቁስ ያጠቃልላል ብለዋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ አይሻ መሃመድ በበኩላቸው፥ የሽብር ቡድኑ የአፋር ክልል በርካታ ንፁሃንን በማፈናቀል የቤት እንስሳትና ንብረታቸውን መዝረፉን ተናግረዋል።

ለተጎጂዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፈጥኖ ሊደርስ ይገባል ያሉት ወይዘሮ አይሻ አሸባሪው ህወሓት ሃገር ለማፍረስ የሚያደርገውን ጥቃት የአፋር ልዩ ሃይልና ህዝቡ እየመከተ ነው ብለዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት ባደረገባቸው የአፋር ክልል በረሃሌ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች በየትምህርት ቤቱና ሆስፒታሉ የተጠለሉ ተጎጂዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።

የበረሃሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት÷ በጥቃቱ ቀያቸውን ለቀው በየሽለቆው ያሉትና በየትምህርት ቤትም ለተጠለሉት አስቸኳይ ድጋፉ መጠናከር አለበት።

በጌታሰው የሺዋስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.