Fana: At a Speed of Life!

የህልውና ዘመቻውን መደገፍ ሃገር እንዳትፈርስ ማድረግ ነው – የሐረሪ ክልል መንግስት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በህልውና ማስጠበቅ ዘመቻ ላይ ተሰልፈው መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎችን መደገፍ ሃገር እንዳትፈርስ ማድረግ መሆኑን የሐረሪ ክልል መንግስት ገለፀ፡፡
ሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ ሃገራችንን ለማፍረስና ህዝቡን ለማዋረድ ተቀናጅተው የከፈቱትን ሁለንተናዊ ጥቃት ለማክሸፍ እና የተጀመሩ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማስቀጠል የሐረሪ ክልል መንግስትና ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊትእንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጎን ተሰልፎ ሁሉን አቀፍ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስሪያ አብደላ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊት እና በህልውና ማስጠበቅ ዘመቻ ላይ ተሰልፈው መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎችን መደገፍ ሃገር እንዳትፈርስ ማድረግ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
“እንደ ክልል ወደ ሰራዊታችንን የሚቀላቀሉ ወጣቶችን መርቀን ሸኝተናል” ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ፥ በቀጣይም ወደ ሰራዊቱ ለመቀላቀል የሚፈልጉ ወጣቶች እየተበራከቱ መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡
የክልሉ ልዩ ሃይልም ወደ ግንባር ሄዶ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
በክልል ደረጃ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች የወር ደመወዛቸውን ለሰራዊቱ ድጋፍ ያደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ÷ በቀጣይም የንግዱ ማህበረሰብና ሌሎች አካላትን ያሳተፈ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.