Fana: At a Speed of Life!

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ።
የድርጅቱ ዳይሬክተር ጄነራል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ እንደተናገሩት፥ የአሸባሪው ህወሓትና ሌላኛው አሸባሪ ተባባሪው ሸኔ ወደመቃብራቸው እስከሚገቡ ድረስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እስከ ዘመቻ የሚደርስ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
እንደ ኮማንደሩ ገለፃ ድርጅታቸው አሸባሪውን ሀይል ለመጣል የራሱን አስተዋፅኦ የሚያደርግ ሲሆን 107 ሰራተኞቹም ወደ ግምባር መዝመታቸውን ጠቁመዋል።
የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሀረር የጦር አካዳሚ አሉሙናይ ማህበርም ለሰራዊቱ ያዋጣውን ከ300 ሺህ ብር በላይ ገቢ አድርጓል።
የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሻምበል በቀለ ፀጋዬም በተመሳሳይ ማህበራቸው ከመንግስትና ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን ጠቁመው አሸባሪው ቡድን ወደ መቀመቅ እስከሚወርድ ድረስ የአቅማቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ከዚህ ቀደም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.