Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብንን ጦርነት መክተን ሕዝባችንን እናኮራለን – ሌ/ጄ ደስታ አብቼ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብንን ጦርነት መክተን ሕዝባችንን እናኮራለን ሲሉ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ገለጹ፡፡

ሌተናል ጄኔራል ደስታ ይህንን ያሉት የመከላከያ ሚኒስቴር ያስገነባው የአዋሽ በርታ የእግረኛ ሻለቃ ካምፕ በተመረቀበት ወቅት ነው ።

ግንባታው ማዘዣ ጣቢያን ጨምሮ የሠራዊት መኖሪያ ቤቶችን ያካተተ ሲሆን÷ አዋሽ በርታ ካምፕ የክሊኒክ ፣ የኢንፎርሜሽ ኮሙዩኒኬሽን፣ የመዋኛ ገንዳና ሌሎች አገልግሎቶችን ለሠራዊቱ እንዲሰጥ ተደርጎ በዘመናዊ መንገድ የተገነባ ነው።

የካምፑ ግንባታ ለሠራዊቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው መሆኑን የገለፁት የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊው÷ ሠራዊቱ የሀገርን ህልውና እያስከበረ ባለበት ወቅት ተጎዳኝ ሥራዎችን በብቃት እየፈጸመ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብንን ጦርነት መክተን ሕዝባችንን እናኮራለንም ብለዋል።

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የዲዛይንና ዋጋ ግምት መምሪያ ሀላፊ ኮሎኔል ያደታ አመንቴ በበኩላቸው፥ መምሪያው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ግንባታዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ገንብቶ እያስረከበ መሆኑን ገልጸዋል።

የካምፑ መገንባት ለሠራዊቱ ከሚሠጠው ቀጥተኛ አገልግሎት በዘለለ በሕክምና፣ በመብራትና በውሃ አቅርቦት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ የበርታ ነዋሪዎች ደስታቸውን ገልፀዋል።

የመከላከያ መሃንዲስ መምሪያ በ11 ወራት ውስጥ የገነባውን ባለ 37 ብሎክ የአዋሽ በርታ የእግረኛ ሻለቃ ካምፕ ለግንባታው ባለቤት ለምሥራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አስረክቧል።

የአዋሽ በርታ የእግረኛ ሻለቃ ካምፕ ከ84 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.