Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ የለገሀር-ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከለገሀር – ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ የሚዘልቀውን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጎበኙ።

በጉብኝት ስነ ስረዓቱ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እና ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ኢንጅነር ታከለ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ለትራፊክ ፍሰቱ ተጨማሪ አማራጭ ከመሆን በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በአፋጣኝ እንዲፈቱ እንደሚደረግ የገለፁት ምክትል ከንቲባው፥ የሚመለከታቸው ተቋማት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

180 ሚሊየን ብር በላይ የተመደበለት የመንግድ ፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 10 ሜትር የጎን ስፋት ይኖረዋል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከለገሀር ወደ ቦሌ ለመጓዝ አማራጭ በመሆን ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።

የለገሀር- ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በሶስት ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.