Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ በአፍጋን የቀሩ ዜጎችን ለማስወጣት ከታሊባን ጋር እየመከረች ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታኒያ በአፍኒስታን የቀሩ የሀገሯን እና ሌሎች ዜጎችን ማስወጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከታሊባን ጋር በኳታር ዶሃ እየመከረች ነው፡፡
 
ውይይቱ ታሊባን አፍጋኒስታንን ለቀው ለሚወጡ ዜጎች ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ማራዘሙን ተከትሎ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
 
በምክክር መድረኩ የብሪታኒያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የታሊባን ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
 
ውይይቱ በሀገሪቱ የሚገኙ የብሪታኒያ ዜጎች አና ከአሜሪካ ጋር ላለፉት 20 ዓመታት ሲሰሩ የነበሩ አፍጋናያውያን ደህንነታቸው ተጠብቆ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እና ዜጎች ወደ ጎረቤት ሀገራት በሰላም በሚወጡበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ተገልጿል፡፡
 
እስካሁን ብሪታንያ ከታሊባን አገዛዝ የሚሸሹ 5 ሺህ ዜጎቿን ጨምሮ17 ሺህ የሚደርሱ የአፍጋኒስታን ዜጎችን ከሀገሪቱ አስወጥታለች፡፡
 
በተመሳሳይ አሜሪካ ከ120 ሺህ በላይ ሰዎችን ከአፍጋኒስታን ማስወጣት መቻሏን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናግረዋል፡፡
 
ምንጭ፦ ቢቢሲ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.