Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ፣ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስና 70ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል ፡፡

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጳውሎስ ካሱ÷ ኢትዮጵያን ለመታደግ አለመስማት ሳያግደን ፣ በብሔርና ሀይማኖት ሳንክፋፈል በአንድነት መቆማችን እኛ ኢትዮጵያውያን በሀገር ጉዳይ አቋማችን አንድ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል ፡፡

ይህም ለኢትዮጵያ ኩራት ለጠላት ደግሞ እፍረት ነው ሲሉ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

የደም ልገሳና የገንዘብ ደጋፉ እንደሚቀጥልና አስፈላገውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ዶክተር ጳውሎስ ካሱ አረጋግጠዋል ፡፡

የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብ/ጀ አስፋው አያሌው÷ ‘ደማችን ለሀገራችንና ለሰራዊታችን’ በማለት ደም በመለገሳቸውና ከሚያገኙት ገቢ ቀንሰው ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.