Fana: At a Speed of Life!

ሸኔ በኦሮሞ ስም የሚነግድ የኦሮሞ ጠላት የሆነ የጥፋት ቡድን ነው – አባ ገዳ ሁንዴ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሸኔ የሽብር ቡድን በኦሮሞ ስም የሚነግድ ትናንት የኦሮሞን ሲገድል ከነበረው የህወሓት የሸብር ቡድን ጋር ጋብቻ የፈጸመ የኦሮሞ ጠላት ነው ሲሉ አባ ገዳ ሁንዴ በየነ ገለጹ።

የኦሮሞ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለሃገር የሚራራ አንጀት የሌለው፣ በእናቶች እንባ የሚደሰት እና ሃገር ስትደማ የሚረካ የከሃዲዎች ስብስብ መሆኑን ነው አባ ገዳ ሁንዴ የገለጹት፡፡

የሽብር ቡድኑ በስልጣን በቆየባቸው ዓመታት ዜጎችን ለእልቂት፣ ሀገርን ለምጣኔ ሃብታዊ መሽመድመድ፣ ወንድማማች የሆኑ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን እርስ በርስ ለማጋጨት ሴራ ዘርግቶ ሲሰራ መቆየቱ ደግሞ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው።

የሽብር ቡድኑ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በታላቅ ክብርና ደስታ በሚከበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ የፈጸመው የዜጎች እልቂት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ዜጎች ለመብታቸው አደባባይ ሲወጡ ምላሹ አፈ-ሙዝ፣ ሃሴቱ ደግሞ የህዝብ ዋይታ መሆኑም እንዲሁ።

አባ ገዳ ሁንዴ የወያኔ ስርዓት ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን ገዳይ፣ አውዳሚ፣ አጥፊና ለትውልዱ የማይበጅ መሆኑን አንስተው÷ በወቅቱ የነበረው ስርዓት በተለይ ለኦሮሞ ወጣት እጅግ አስከፊ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡

ትላንት የኦሮሞን ህዝብ ሲጨፈጭፉ የነበሩት የሸኔና የወያኔ የሽብር ቡድኖች ዛሬ በጋራ እንደሚሰሩ ይፋ ማድረጋቸው አዲስ ጉዳይ አለመሆኑንና የሽብር ቡድኖቹ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት መሆናቸውን ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።

የሸኔ የሽብር ቡድንም በኦሮሞ ስም የሚነግድ ትናንት ኦሮሞን ሲገድል ከነበረ ቡድን ጋር ጋብቻ የፈጸመ ለኦሮሞ የማይበጅ የጥፋት ኃይል መሆኑን አንስተዋል።

የኦሮሞ ወጣት መስዋትነት የከፈለላትን ኢትዮጵያ ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ለህልውናዋ መዋደቅ እንዳለበትም አባ ገዳ ሁንዴ በየነ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.