Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ፍኖተ ካርታ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፉን ክፍተቶች ታሳቢ ያደረገ ነው-ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ ፍኖተ ካርታ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፉን ክፍተቶች ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገለጹ፡፡

አዲሱ ፍኖተ ካርታ ከዚህ ቀደም በነበረው ስርዓት ትምህርት ላይ የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላ እና በጥናት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ለመቅረፅ በተደረገው ጥናት የትምህርት ጥራት፣ የተማሪዎች ግብረ ገብነት፣ የትምህርት ስርዓቱ ከኢኮኖሚው ጋር አለመጣጣም እና የትምህርት ዘርፉ በቴክኖሎጂ አለመዘመኑ ጥናቱ ያመላከታቸው ክፍተቶች መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

አዲሱ ፍኖተ ካርታም እነዚህን ክፍተቶች የሚሞላ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ከዝግጅት አኳያ ስርዓተ ትምህርቱን በ2014ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር ዝግጁነት ቢኖርም በበጀት እጥረት ምክንያት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ለመግባት እንዳልተቻለ አንስተዋል፡፡

በዚህም በ 2014ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ የሙከራ ትግበራ እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላከታል፡፡

በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ጥናት እና ዝግጅት አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከ200 በላይ ምሁራን መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.