Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንከፍላለን-የከፋ ዞን ሴቶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገር ክብርና ለህዝብ ሰላም በግንባር እየተዋደቀ የሚገኘውን መከላከያ ሰራዊት ለመደገፍ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የከፋ ዞን ሴቶች ገለጹ፡፡

የዞኑ ሴቶች ለሁለተኛ ጊዜ ለመከላከያ ሠራዊቱ በቀላሉ የማይበላሹ ስንቆችን በማዘጋጀት ላይ ናቸው።

በተጨማሪም ለሴት መከላከያ ሰራዊት አባላት የሚሆን ሳሙናና ሌሎችም የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አዘጋጅተዋል።

የዞኑ ሴቶች መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ እያሳዩት ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት የዞኑ የሃብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ወይዘሮ ሕይወት አሰግድ÷ በ2ኛው ዙር ለመከላከያ ሰራዊቱ በሚደረገው የስንቅ ዝግጅት ከ 800 ሺህ ብርቱካን በላይ ወጪ መደረጉን ገልጸዋል።

እስካሁን ባለው የድጋፍ ሂደት በዞኑ በአይነት፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ከ35 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን÷ለመከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በቅድስት በርታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.