Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር ደሴ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር ደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከተለያዩ የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ 800 ቤተሰቦች ድጋፍ አድርጓል።

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መላኩ ቸኮል ድጋፉ ከዓለምአቀፉ ቀይመስቀል ኮሚቴ መገኘቱን የገለጹ ሲሆን÷ በቀጣይ ቀናትም ለ6ሺህ ቤተሰብ የሚደርስ ይሆናል ብለዋል ።

በድጋፍ አሰጣጡ ላይ የተገኙት የዓለምአቀፉ ቀይመስቀል ኮሚቴ ኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ አቶ ዘውዱ አያሌው በበኩላቸው÷ ለተፈናቃዮች ብቻ ሳይሆን በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት የአገልግሎት ጫና ለደረሰባቸው 13 የህክምና ተቋማት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

ለድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የሆስፒታል አልጋዎች፣ ዊልቼሮችና ፍራሾች ናቸው በድጋፍ የተሰጡት።

ዓለምአቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ ተግባርና ሃላፊነቱ በጦርነትና ግጭት ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ ነውና ችግሩ እስካለ ድረስ ድጋፍ ማድረጋችንን እቀጥላለን ብለዋል።

በእሌኒ ተሰማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.