Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከአፋር ለተፈናቀሉ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ላከ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ለተጠለሉ ወገኖች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ መላኩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለምሸት ተሾመ እንደገለጹት÷ ከተለያዩ የአፋር ክልል አካባቢዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተጠለሉ ዜጎች ነው ድጋፉ የተደረገው።

ድጋፉ 150 ፍራሽ ፣ 200 ብርድ ልብስ ፣ 200 ጥንድ አንሶላ፣ ባለ 20 ሊትር 100 ጀሪካን የምግብ ዘይት ፣ ባለ 25 ኪሎ 70 ከረጢት ሩዝ ፣ ባለ 25 ኪሎ 70 ከረጢት መኮረኒ፣ 50 ካርቶን ፓስታ እና በዩኒቨርሲቲው የተመረተ ባለ 5 ሊትር 100 ጀሪካን ፈሳሽ ሳሙና ነው።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት ሳምንት በፊት ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች በጥፋት ቡድኑ ጉዳት ደርሶባቸውና ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በወሎ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ በስፍራው ተገኝቶ ማስረከቡን አስታውሰዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.