Fana: At a Speed of Life!

በሃዋሳ ከተማ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃዋሳ ከተማ በ2013 በጀት ዓመት 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ፡፡

ይህም ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ445 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አቶ ታምሩ ተፈሪ የከተማውን ገቢ ከመሰብሰብ አንፃር በርካታ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በ2014 በጀት አመት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ከከተማው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.