Fana: At a Speed of Life!

እስካሁን ለመከላከያ ሠራዊት 3 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን ባለው ሂደት ለመከላከያ ሠራዊቱ 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ለሰራዊቱ የተደረገውን የሃብት ማሰባሰብ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም እስካሁን ባለው ሂደት ለመከላከያ ሠራዊት 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ነው የገለጹት፡፡
ከዚህ ውስጥም 42 ሚሊየን ብር የሚሆነው ከዲያስፖራው ማህበረሰብ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
በተጨማሪ 6 ሺህ 679 ሠንጋዎች፣ ከ10 ሺህ በላይ በግና ፍየል፣ በርካታ ብር ግምት ያለው ደረቅ ሬሽን ለሠራዊቱ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
የፌዴራል መንግስት፣ የፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የንግድ ማህበረሰቡ እና ሌሎች ተቋማት አሁንም ለሠራዊቱ ድጋፍ ያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ህልውና መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ማቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.