Fana: At a Speed of Life!

ጥራት ያላቸው እና የሕብረተሰቡን ችግሮች መፍታት የሚችሉ ምርምሮች ሊሰሩ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጥራት ያላቸው እና የሕብረተሰቡን ችግሮች መፍታት የሚችሉ ምርምሮች ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ባዘጋጀው የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ግምገማ ጉባኤ ላይ 218 የምርምር ንድፈ ሃሳቦች ለግምገማ ቀርበዋል፡፡

ንድፈ ሃሳቦቹን ለመገምገም ዩኒቨርሲቲው ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ሲሆን÷ ከዚህ ቀደም የተሰሩት ሪፖርት ተደርገዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተሰሩ የጥናት ስራዎችም የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና አገልግሎቶች ተቀርፀው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር አደም ከድር÷ የህብረተሰቡን ትክክለኛ ችግር የሚፈቱና ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኙ ምርምሮች እንዲሰሩ የአሁኑ ግምገማ ማስፈለጉን ገልፀዋል፡፡

በምርምር ዘርፍ 133 በማህበረሰብ አገልግሎት 85 ንድፈ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን÷ ትክክለኛነታቸው እና ሳይንሳዊ ጥራታቸው የጠበቁት ተመርጠው እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

ዶክተር አደም አክለው ሀገር በቀል እውቀትንና የባህል ሳይንስን የሚያሳድጉ ምርምሮች በዩኒቨርሲቲው ትኩረት እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል።

ንድፈ ሃሳቦቹ ከተለዩ እና ከተገመገሙ በኋላ ወደ ምርምር ስራው ለመግባት 38 ሚሊየን ብር በጀት መያዙንም ለማወቅ ተችሏል።

በቅድስት ዘውዱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.