Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በርካታ የሚሊሻ አባላት ወታደራዊ ስልጠና በመከታተል ላይ ይገኛሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንኛውም ሰዓት ለሚደረግ ሀገራዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በርካታ የሚሊሻ አባላት ወታደራዊ ስልጠና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ የደቡብ ክልል ሚሊሻ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ የሀገርን ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ፈቃደኛ የሆኑ የሚሊሻ አባላት ናቸው ወታደራዊ ስልጠናውን በመከታተል ላይ የሚገኙት።

ስልጠናው በ13 ዞኖች እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች እየተሰጠ ሲሆን ÷ከ50 በላይ ማሠልጠኛ ማዕከላት የሚሊሻ አባላትን ተቀብለው እያሰለጠኑ ይገኛሉ።

የደቡብ ክልል ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀይሌ ዳዊ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በርካታ የሚሊሻ አባላት ስልጠናውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በማንኛውም ሰአት ለሚደረግ ሀገራዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችሉ የሚሊሻ አባላትን ማዘጋጀት የወታደራዊ ስልጠናው አላማ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው እስከዚያው ድረስ ግን የአሸባሪው ሀይል ተላላኪዎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርሱት ጥፋት እንዳይኖር አካባቢያቸውን በንቃት እንደሚጠብቁም ነው የገለጹት።

በክልሉ በቀጣይም ሰልጣኞች ወደ ማዕከላት ገብተው ስልጠና የሚወስዱ ይሆናል።

በሞሊቶ ኤልያስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.