Fana: At a Speed of Life!

በወረባቦ ሰርጎ ገብቶ የነበረው ቁራጭ የህወሓት ሃይል እየተደመሰሰ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በወረባቦ ወረዳ ሰርጎ ገብቶ የነበረው ቁራጭ የጁንታው ሃይል እየተደመሰሰ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
 
የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ መሃመድ ሰይድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ተንቀዥቅዦ ወደ ወረዳው ገብቶ የነበረው ቡድን በመከላከያ፣ በአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ አባላትና በማህበረሰቡ እየተደመሰሰ ነው፡፡
 
ጁንታው ወረዳውን ለቆ መሸሹን የገለጹት ሀላፊው÷ የጸጥታ ሃይሉ በገባበት እየተከተለ እየቀበረው መሆኑን ነው የገለጹት።
 
በየትኛውም በኩል ማምለጫ የሌለው የጁንታው ሃይል አማራጩ መደምሰስ ብቻ መሆኑን አቶ መሃመድ ተናግረዋል።
 
ወጣቶች በግንባር ለሚገኘው የጸጥታ ሃይል ከኋላ ደጀን በመሆን ከከተማው ማህበረሰብ ምግብ በማሰባሰብ ግንባር ድረስ በማድረስ ለሰራዊቱ ያለውን ደጀንነት በተግባር እያሳዩ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በተጨማሪም ከጠላት ሃይል ጋር በሚደረገው ፍልሚያ የወረዳው ወጣቶች በከፍተኛ ወኔና ተነሳሽነት ያላቸውን መሳሪያ በመያዝ በጦር ግንባር ድረስ በመግባት የጠላት ሃይል ጋር እየተፋለመ ይገኛል፡፡
 
በከድር መሃመድ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.