Fana: At a Speed of Life!

ከ50 ዓመታት ወዲህ ከዓየር ንብረት ለውጥ ጋር የተገናኙ አደጋዎች በ 5 እጥፍ ጨምረዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ50 ዓመታት ወዲህ በዓለም በተስተዋለው የዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈጥሮ አደጋዎች በአምስት እጥፍ መጨመሩን የዓለም ሚቲዮሮሎጂ ድርጅት ገለፀ፡፡

ድርጅቱ በመብረቅ፣ በጎርፍ እና በድርቅ አደጋዎች ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እንደቀነሰ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እንደ ተመራማሪዎች ገለፃ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ የቻለው አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት የተሻለ የትንበያ እና የማሳወቂያ ስርዓት በመዘርጋቱ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከአስር ዓመታት ወዲህም የዓለም ሙቀት እየጨመረ በመምጣቱ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተዛመዱ አደጋዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል ነው ያለው ድርጅቱ፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1970 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት 11 ሺህ ያህል አደጋዎች እንደተከሰቱ የዓለም ሜቲዮሮሎጂ ድርጅት አመላክቷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.