Fana: At a Speed of Life!

የደሴ ባለሃብቶች ለመከላከያ ሰራዊት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በደሴ ከተማ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ለመከላከያ ሰራዊት ፣ለልዩ ሃይልና ሚሊሽ 1ሚሊየን 463 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 1ሚሊየን 358 ሺህ ብሩ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ÷ 105 ሺህ ብሩ ደግሞ በአይነት የተደረገ ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሉሲ፣ ጎልደን እና ታይም ሆቴል እያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በነገው ዕለትም ባለሃብቶቹ ግንባር ድረስ በአካል በመገኘት የጸጥታ አካላቱን እንደሚያበረታቱ ተናግረዋል፡፡

በዘሩ ከፈለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.