Fana: At a Speed of Life!

የተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ ስርጭት በመቀነስ የዋጋ ንረቱን ያረጋጋል-ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣው የፖሊሲ ማሻሻያ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ ስርጭት በመቀነስ የዋጋ ንረቱን ማረጋጋት እንደሚስችል የምጣኔ ሃብት ምሁራን ተናገሩ ፡፡
 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር እና ተመራማሪው አቶ ምትኩ ከበደ እንደገለጹት ÷እርምጃው ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና የገንዘብ መግዛት አቅምን በማሳደግ አሁን ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ግሽበት ለማረጋጋት ያስችላል፡፡
 
ማሻሻያው ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡትን ዋስትና ይጨምራል ያሉት አቶ ምትኩ ÷ ዳያስፖራዎች ገንዘባቸውን በሃገር ውስጥ እንዲያስቀምጡ የሚያበረታታ መሆኑም አንስተዋል፡፡
 
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጌታቸው በበኩላቸው÷ መንግስት አላስፈላጊ ወጪዎችንበ መቀነስ በቁጥር አናሳ የሆኑ ነጋዴዎችን መቆጣጠር እና ገበያውን ማረጋጋት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
 
ባንኮች የመጠባበቂያ መጠን እና የሚበደሩትዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከፍ ማለቱ በባንኮች የሚንቀሳቀሰውን የገንዘብ መጠን እንዲቀንስ ደርጋልም ነው ያሉት፡፡
 
መንግስት አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ እና ተጨማሪ እርምጃዎችን በመውሰድ የዋጋ ንረቱን ማረጋጋት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ምሁራኑ አሳስበዋል፡፡
 
በአልማዝ መኮንን
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.