Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ለተፈናቃይ ወገኖች የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች በደሴ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖች ያሉበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል።

ከሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የትህነግ ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖች በደሴ ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።

ተፈናቃዮቹ የደሴ ከተማ ሕዝብ እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ የሚመሰገን መሆኑን ገልፀው÷ በመንግሥት በኩል ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

አሸባሪው ትህነግ ቤት ንብረታችን ላይ ጉዳት አድርሷል÷ በቀጣይ በዘላቂነት የምንቋቋምበት ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርልን ይገባል ሲሉም የሥራ ኃላፊዎቹን ጠይቀዋል።

ከተፈናቃዮቹ ለተነሳላቸው ጥያቄ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሐሰን አካባቢያቸው ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ሲመለስ ቤት ንብረታቸው የወደመባቸውን ወገኖች መንግሥት ከክልሉ ጋር በቅንጅት የመልሶ ማቋቋም ሥራ እንደሚያከናውን ተናግረዋል።

የደሴ ከተማ ሕዝብ ለወገኖቹ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ያሉት የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጅአለም ተፈናቃዮቹ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ከደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጋር የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.