Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም የህወሓት ተላላኪዎችን አሳልፎ መስጠት አለበት – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ክልሉን ለማተራመስ የሚሹ የህወሓት ተላላኪዎችን አሳልፎ በመስጠት የድርሻው እንዲወጣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጥሪ አቀረቡ።
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ከማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል ።
የህወሓት ተላላኪዎች በጋምቤላ ከተማ የፈጠሩት ሽብር የእርስ በእርስ ማለትም የአኚዋክና የኑዌር ግጭት አድርገው ለማተራመስ ቢፈልጉም በመንግስትና በህዝብ ጥረት ከተማውን ማረጋጋት መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ድርጊቱን የፈፀሙትን በተዘዋሪም ሆነ በቀጥታ እጃቸው ያለበት ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ የክልሉ መንግስት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ በየደረጃው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የየድርሻቸውን በመወጣት ለመንግስት ጥቆማ በመስጠት የጋራ የሆነውን ሰላም መጠበቅ እንደሚቻል አብራርተዋል።
ወጣቱ ሀገሩንና አካባቢውን በመጠበቅ ረገድ ሚናው ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን በማያውቀው እሳት ውስጥ እራሱን አሳልፎ መስጠት እንደሌለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ወላጆች በአካባቢያቸው የሚመለከቱትን አላስፈላጊ ድርጊቶች በአጭሩ መግታት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ከተማዋን የሰላም ከተማ ለማድረግ ሁሉም የየድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
አሸባሪዎቹ ዋና አላማቸው ሁለቱ ብሔረሰቦችን ግጭት ለመፍጠር ሲሆን፥ ይህንን ደግሞ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ህዝቡ ሊጠነቀቅ ይገባል ያሉት ደግሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታንኳይ ጆክ ናቸው።
ህውሓት ፣ ሸኔ እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር የተባሉት የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ በጋራ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በውይይቱ ተነስቷል።
በውይይቱ ላይም የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶች ሴቶች የሀይማኖት አባቶች በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች መሳተፋቸውን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታርያት ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.