Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አውቶብሶቹን ከማዕከል ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችል መከታተያ ሊገጠም ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንበሳ የከተማ አውቶብስ ስምሪት የወጡ አውቶቡሶቹን ከማዕከል ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችል መከታተያ ለመግጠም ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
መከታተያው አውቶብሶቹ የት መስመር ላይ እንዳሉ እና ረጅም ጊዜ ያለ ስራ እንዳይቆሙ የምልልስ ፍጥነቱን ለማስተካከል እንደሚያግዝ በድርጅቱ የብዙኀን ትራንስፖርት ስምሪት እና ቁጥጥር ዋና ኃላፊ አቶ መላኩ ካሳዬ ተናግረዋል።
ከሰሞኑ በመስመር ቁጥር 30 አውቶብስ ላይ አላግባብ የዋጋ ጭመሪ ተደርጓል በሚል ለቀረበው ቅሬታም፥ ከዛሬ ጀምሮ በመስመሩ ላይ የታሪፍ ማስተካከያ በማድረግ ከ8 ብር እስከ 5 ብር እንደ ርቀቱ ተሳፋሪዎች እንዲጠቀሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ ጀምሮ መንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ባወጣው ታሪፍ አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
ለአዲስ ዓመትም ተማሪ ስለሚኖር የትራንስፖርት ተጠቃሚው ቁጥር እንደሚጨምር በማሰብ በተለያየ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የቆሙ አውቶብሶችን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ድርጅቱ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በ125 መደበኛ እና በ10 ልዩ መስመሮች የብዙኀን ትራንስፖርትአገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.