Fana: At a Speed of Life!

የአማራና ቅማንት ህዝቦች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአማራና የቅማንት ህዝቦች ዘመናትን ያስቆጠረ ወንድማማችነትና እህትማማችነት በፅንፈኞችና በፀረ ኢትዮጵያውያን ሀይሎች አይበረዝም” በሚል መርህ የአማራና ቅማንት ህዝቦች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ፥ ሁለቱ ህዝቦች ለዘመናት አብረው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

አያይዘውም ህወሓትን መሰል ሽብርተኛ ቡድኖች መጠቀሚያ ሊያደርጉት የሚችሉት ሀይል እንደሌለ ሊያውቁ ይገባል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ያለው ከኢትዮጵያ ጎን የቆሙ እና ከህወሓት የሽብር ቡድን ጎን የቆሙ ሃይሎች መኖራቸውን አስረድተዋል።

አያይዘውም ጠላት የተለያዩ ግንባሮችን በማብዛት ሀገርን ለማፍረስ እየጣረ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይ ፊት ለፊት ካለው ግንባር በተጨማሪ የቅማንት እና የአማራ ህዝቦችን በማጋጨት እና ብጥብጥ በመፍጠር ሱዳን ያለውን ሀይልና ትጥቅ የማስገባት ህልም ስላለው እድል መስጠት እንደማይገባም አንስተዋል።

እንደዚህ አይነት እድሎች እንዳይፈጠሩ መንግስት ከፍተኛ ስራወችን እየሰራ መሆኑን በመጥቀስም፥ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የህወሓት ሴራ እንዳይሰራ ለማድረግ የሰላም አማራጮችን መጠቀም እንደሚገባም አውስተዋል።

መድረኩ ህዝቡ አንድ ሆኖ ከመንግስት ጎን በመቆም አብሮ እንዲታገል በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ህዝቡ ለፀጥታ ሀይሎች ደጀንነቱን በማሳየት በውስጡ ያሉ የሽብር ቡድኑ ደጋፊ ሀይሎችን በመጠቆም አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል ተብሏል።

በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሃይሎች አፈናወችን በማካሄድ፣ መንገድ በመዝጋት እንዲሁም በመከላከያ እና የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ላይ ጥቃቶችን በመሰንዘር ሁለቱን ህዝቦች ለማጋጨት እየሞከሩ እንደሚገኙም በመድረኩ ተነስቷል።

ከዚህ አንጻርም ህዝቡ ከእነዚህ ሀይሎች በመነጠል ሊታገላቸውና አሳልፎ ሊሰጣች እንደሚገባም አፈ ጉባኤው ጠይቀዋል።

በኤልያስ አንሙት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.