Fana: At a Speed of Life!

የጅቡቲ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ዝግጁ ነው- የጅቡቲ የትራንስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጂነር የኋላሼት ጀመረ ከጅቡቲው የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሀውመድ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀም ላይ በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ በቅንጅት ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም ደህንነቱ የተጠበቀ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ አሰራሮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጂነር የኋላሼት÷ በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ በ10 ዓመቱ ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን በአጠቃላይ የሎጅስቲክስ ጊዜና ወጪን በመቀነስ የሀገሪቱን የሎጅስቲክስ ውጤታማነትን ለማሻሻል በቅንጅትና በመናበብ መስራት ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል።
የጅቡቲ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሀውመድ በበኩላቸው÷ የጅቡቲ መንግስትም በጋራ ተቀናጅቶ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ማብራራታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.