Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ከተማ የ4ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ – ቴሌኮም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ ሪጅን ጋምቤላ ከተማ የአራተኛ ትውልድ /4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ / ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት አካሄደ ።

የሞባይል ኢንተርኔት በላቀ ፍጥነት ለመጠቀም የሚያስችለውን የ”4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ” በሪጅኑ 93 ሺህ 407 ደንበኞች ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው በሀገሪቱ የተለያዩ 103 ከተሞች የአራተኛ ትውልድ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማስፋፋት አቅዶ በመንቀሳቀስ ጋምቤላን ከተማ ጨምሮ 73 ከተሞችን የአገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል።

ኩባንያው በተያዘው የበጀት ዓመታ 106 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

በስነ- ስርዓቱ ላይ የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.