Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
ፍኖተ ካርታው ከ2013 እስከ 2027 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ ነው ተብሏል።
የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ፥ለ15 ዓመታት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በጤናው ዘርፍ መከላከልን መሰረት ላደረገው የጤና ስትራቴጂ ትልቁን ሚና ሲጫወት መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
እንደሀገር የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ከተጀመረ በኋላ በጤናው ዘርፍ ድሎች መመዝገባቸውንና በተለይ የእናቶች እና የህፃናት ሞትን መቀነስ መቻሉ ተናግረዋል።
በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች 17 ሺህ ጤና ኬላዎች እንደተገነቡና በሁሉም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች መመደባቸውን ጠቁመዋል።
ለፕሮግራሙ ያለውን ፋይዳ በመገንዘብና እየጨመረ ከመጣው የህዝብ ቁጥር እና ግንዛቤ ጋር የተጣጣመ የጤና ኤክስቴንሽን ተግባራዊ ለማድረግ ፕሮግራሙን ማሻሻል ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው፡፡
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሃመድ፥ ባለፉት 15 ዓመታት ፕሮግራሙ የአካባቢውን ማህበረሰብ ህይወት የቀየረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የክልሉን የጤና ዘርፍ ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፥ የክልሉ መንግሥት በሁሉም የጤና ዘርፎች ላይ የሚደረጉ ስራዎች ላይ በቁርጠኝነት ይሳተፋል ማለታቸውን የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.