Fana: At a Speed of Life!

የሐዋሳ ሐይቅን ለመታደግ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሐዋሳ ሐይቅን መታደግ በሚቻልበት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት ተፈጥሮን ያማከለ የአረንጓዴ መሠረተ ልማት ሥራዎችን በመዘርጋት የሐዋሳ ሐይቅ ላይ የተጋረጠውን ስጋት መቅረፍ እንደሚቻል አመላከተ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከፌደራል ተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን፣ ከጂአይዜድ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሐይቁን መታደግ በሚቻልበት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂዶ የመስክ ምልከታ ፕሮግራም አከናውኗል፡፡

የፌደራል ተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ዳይሬክተር ዶክተር አዳነች ያሬድ ÷ ስምጥ ሸለቆ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች ያሉ የኢትዮጵያ ሐይቆች፣ በርካታ ጥቅም እየሰጡ የሚገኙ የተፈጥሮ ሐብቶች ናቸው ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሯ በንግግራቸው በተፋሰሱ ላይ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ተግዳሮቶች እየደረሱ እንደሚገኝም ጠቁመው፥ ተግዳሮቶችን ስልታዊ በሆነ መንገድ ለመፍታትና ለመቀነስ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ በትብብር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ዶክተር ሙሉጌታ ዳዲ፥ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የPLH-NaGI ፕሮጀክት አስተባባሪና ተመራማሪ የፕሮጀክቱን ዝርዝር ዓላማ እና አፈፃፀም መግለፃቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.