Fana: At a Speed of Life!

የሻኪሶ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞችና አመራሮች ለህልውና ዘመቻው ድጋፋቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሻኪሶ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞችና አመራሮች÷ አሸባሪው ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከትና በደጋፊ አስፈፃሚዎቹ የሚያደርሰውን የኢኮኖሚ አሻጥር ለማጋለጥና ለመከላከል ሁለንተናዊ ድጋፋቸውን እንደማይቋርጡ ገለጹ፡፡

የከተማው አስተዳደር ሰራተኞችና አመራሮች የሕይወት መስዋዕትነት የሚያስከፍል ቢሆንም በሀገር ሉአላዊነት ላይ እንደማይደራደሩ መግለጻቸውም ተመላክቷል።

ሀገር ለማፍረስ በኢኮኖሚ አሻጥርና ፊት ለፊት የተከፈተውን ጦርነት ለመመከትም የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ነው የተገለፀው፡፡

የሀገር ሉአላዊነትን ለማስከበር የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው ሰራዊት ደም መለገስ፣ ስንቅ ማዘጋጀትና ገንዘብ መለገስ የሚያንስ እንጂ የሚበዛ እንዳልሆነም ነው የገለጹት፡፡

የሻኪሶ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነጌሳ ዱጎም ከሰራተኞቹና አመራሮች ለሠራዊቱ ድጋፍ የሚውል 800 ሺህ ብር ቃል መገባቱን ጠቁመዋል።

ቀደም ብሎ ሰራተኞቹና አመራሮቹ 130 ሺህ ብር እንደለገሱ አስታውሰው፣ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለአሁኑ የህልውና ዘመቻ 11 የእርድ እንስሳትን ማዘጋጀታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

 

 

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.