Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሴቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ስንቅ ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ ግንባር ድረስ ባለው የክተት ጥሪ የሴቶች ሚና ላቅ ያለ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ይህ የተገለፀው በደሴ ከተማ “አንድ ሁነን ጠንካራ ድምፅ እናስተጋባለን አንድ ሁነን በጠንካራ ክንድ እናሸንፋለን” በሚል መሪ ቃል የህልውና ዘመቻው ከሴቶች ተሳትፎ አንፃር በሚዳስስ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ ሴቶች እንደገለፁት፥ እስከ ግንባር የሚዘምቱ ልጆቻቸውን እና የትዳር አጋሮቻቸውን ከማበረታታትና ከመሸኘት ባለፈ እነሱም በቂ ወታደራዊ ስልጠናን ወስደው ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የደሴ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሀላፊ የሆኑት ወይዘሮ ኤልሳቤት አለሙ በበኩላቸው፥ በደሴ ከተማ ደረጃ የህልውና ዘመቻው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሴቶች በሁሉም ዘርፍ የህልውና ዘመቻው የኋላ ደጀንነታቸውን በማሳየት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በቀጣይም ሴቶች በተቀናጀ መልኩ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ የክተት ጥሪ በመድረኩ ተዘጋጅቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አባይነህ መላኩ፥ ሴቶች በህልውና ዘመቻ ላይ ያላቸው ተሳትፎና ስኬት በታሪክም ጭምር የሚጠቀስ ነው ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ስንቅ ከማዘጋጀት ባለፈ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ለመከላከያ ሀይሉ የኋላ ደጀን ለመሆን የሴቶች ሚና ጉልህ ነው ብለዋል፡፡
እንደዚህ አይነት የንቅናቄ መድረኮች በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተጠቁሟል፡፡
በይከበር አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
3,131
People Reached
179
Engagements
Boost Post
133
7 Comments
4 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.