Fana: At a Speed of Life!

ለወገን መኖርን በተግባር የኖሩ…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰይድ ጉማቴ 106 የሚሆኑ በግጭት ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ወገኖች በቤታቸው አስጠልለዋል።

ወይዘሮ ሀድራ ኑርየ÷ ከመርሳ ተፈናቅላ የመጣች የስምንት ወር ነፍሰ ጡር ስትሆን ደጉ አባት ቤታቸው ካለው የሰው ቁጥር አንፃር አይመቻትም በማለት ቤት ተከራይተው አስፈላጊ ነገሮችን አሟልተው እያኖሯት እንደሆነ ተናግራለች።

በጎነትን ነው ለልጅ ማውረስ የሚሉት አቶ ሰይድ ጉማቴ በቤታቸው ካስጠለሏቸው በተጨማሪ 50 ለሚሆኑት ቤት ተከራይተው እንዲኖሩ እያደረጉ ይገኛል።

ሁላችንም ተባብረን ይህንን ቀን ማለፍ አለብንም ሲሉ መልካም ምክራቸውን ሰጥተዋል – መልካሙ አባት አቶ ሰይድ ጉማቴ።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.