Fana: At a Speed of Life!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው 21 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ነው ድጋፍ ለማድረግ የወሰኑት።

አመራሮቹና ሰራተኞቹ የአንድ ወር ደመወዛቸውን በመለገስ ድጋፉን ለማድረግ ውሳኔውን ማሳለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ በወቅቱ እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡም ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ለደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በድጋፍ መስጠቱን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.