Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በአፋር በርሃሌ ወረዳ በከፈተው ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጎድተዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአፋር በርሃሌ ወረዳ በከፈተው ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጎድተዋል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በጥይት እሩምታ ቆስለው በአብዓላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል፡፡

ቁስለኞቹ በከባድ መሳሪያ እና በስለት ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን ነርስ ኪያር አሊ ተናግሯል፡፡

ተጎጂ ቁስለኞች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት አሸባሪው ህወሓት በምሽት ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት ንፁሃኑን ገድሏል፡፡

ከቁስለኞቹ መካከል ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እስካሁን የማያውቁ መኖራቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

ህክምናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ቁስለኞች የቡድኑ ጭካኔ ለህፃናት እንኳን ርህራሄ የሌለው ነው ብለዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰና ጌታሰው የሺዋስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.