Fana: At a Speed of Life!

ከ44 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ቁሳቁሶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 1 እስከ 20/2013 ድረስ ከ44 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ናቸው ተብሏል፡፡

በዚህም የገቢ ኮንትሮባንድ 38 ሚሊየን 964ሺ 200ብር÷ ወጪ ደግሞ 5ሚሊየን 383ሺ 287ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በድምሩም የ44ሚሊየን 347ሺ 487ብር ግምት አላቸው ነው የተባለው፡፡

ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኮንትሮባንድን የመቆጣጠር ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.